ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 13:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቶአል፤ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤

2. እናንተ የምታውቁትን፣ እኔም ዐውቃለሁ፤ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።

3. ነገር ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፤ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እሻለሁ።

4. እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናቸሁ፤ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።

5. ምነው ዝም ብትሉ!ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር!

6. እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፤የከንፈሬንም አቤቱታ አድምጡ።

7. ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን?ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን?

8. ለእርሱ ታደላላችሁን?ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?

9. እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን?ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን?

10. በስውር አድልዎ ብታደርጉ፣በርግጥ እርሱ ይገሥጻችኋል።

11. ግርማው አያስደነግጣችሁምን?ክብሩስ አያስፈራችሁምን?

12. ምሳሌዎቻችሁ የዐመድ ምሳሌዎች ናቸው፣መከላከያችሁም የጭቃ ምሽግ ነው።

13. “ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር፤የመጣው ይምጣብኝ።

14. ሥጋዬን በጥርሴ፣ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 13