ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 9:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዮርዳኖስ ምዕራብ ባለው በተራራማው አገር፣ በቈላማው ምድር እንዲሁም እስከ ሊባኖስ በሚደርሰው በመላው በታላቁ ባሕር ዳርቻ የነበሩት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያን፣ የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፣

2. ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ።

3. የገባዖን ሰዎች ግን ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ላይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፣

4. ለማታለል ፈለጉ፤ ስለዚህም ያረጀ ስልቻና የተጣፈ አሮጌ የወይን ጠጅ አቊማዳ በአህያ የጫነጀ መልእክተኛ መስለው ሄዱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 9