ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 5:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚህ ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ያሉት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፣ በባሕሩም ዳርቻ ያሉ የከነዓናውያን ነገሥታት በሙሉ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን እስክንሻገር ወንዙን በእስራኤላውያን ፊት እንዴት እንዳ ደረቀው በሰሙ ጊዜ፣ ልባቸው በፍርሃት ቀለጠ፤ እስራኤላውያንንም ለመቋቋም ድፍረት አጡ።

2. በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቊረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው።

3. ስለዚህ ኢያሱ የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅቶ በጊብዓዝ ዓረሎት በተባለ ስፍራ እስራኤላውያንን ገረዛቸው።

4. እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ።

5. ከዚያ የወጡት ሰዎች ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በጒዞ ላይ ሳሉ የተወለዱት ግን በሙሉ አልተገረዙም ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 5