ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 4:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ከተሻገረ በኋላ፣ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤

2. “ከሕዝቡ መካከል ከየነገዱ አንዳንድ ሰው፣ በድምሩ ዐሥራ ሁለት ሰው ምረጥ፤

3. እንዲሁም ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ልክ ካህናቱ ከቆሙበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ አንሥተው በመሸከም ከእናንተ ጋር እንዲሻገሩና ዛሬ በምታድሩበት ቦታ እንዲያኖሯቸው ንገራቸው።”

4. ስለዚህ ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የሾማቸውን ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ፤

5. እንዲህም አላቸው፤ “ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤል ነገድ ቊጥር አንዳንድ ድንጋይ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤

6. ይህም በመካከላችሁ ምልክት እንዲሆናችሁ ነው። ወደ ፊት ልጆቻችሁ፣ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው ቢጠይቋችሁ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 4