ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 21:33-45 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ለጌድሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

34. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣

35. ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

36. ከሮቤል ነገድ፣ቦሶር፣ ያሀጽ፣

37. ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

38. ከጋድ ነገድ፣በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣

39. ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፦

40. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

41. እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ባጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ።

42. እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው ማሰማሪያዎች ነበሯቸው፤ ማሰማሪያ የሌለው ከተማ አልነበረም።

43. ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ እነርሱም ምድሪቱን ወረሱ፣ መኖሪያቸውም አደረጓት።

44. እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ አንድም ጠላት ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጥቶአቸዋልና።

45. እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከሰጠው መልካም የተስፋ ቃል አንዳችም አልቀረም፤ ሁሉም ተፈጽሞአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 21