ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 21:32-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ከንፍታሌም ነገድ፣በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

33. ለጌድሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

34. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣

35. ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

36. ከሮቤል ነገድ፣ቦሶር፣ ያሀጽ፣

37. ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

38. ከጋድ ነገድ፣በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣

39. ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፦

40. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 21