ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 21:22-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሠማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጡአቸው።

23. እንዲሁም ከዳን ነገድ ኤልተቄን፣ ገባቶን፤

24. ኤሎንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው።

25. ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው።

26. እነዚህ ዐሥር ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ለተቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ተሰጧቸው።

27. የጌርሶን ወገኖች ለሆኑት ለሌሎቹ የሌዊ ጐሳዎች የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ከምናሴ ነገድ እኩሌታ በባሳን ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ጎላንና በኤሽትራ እነዚህ ሁለት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

28. ከይሳኮር ነገድ፣ቂሶን፣ ዳብራት፣

29. የርሙትና ዓይን ጋኒም፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

30. ከአሴር ነገድ፣ሚሽአል፣ ዓብዶን፣

31. ሔልቃትና ረአብ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

32. ከንፍታሌም ነገድ፣በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

33. ለጌድሶናውያን ጐሣዎች የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

34. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተሰጧቸው የሚከተሉት ናቸው፤ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓም፣ ቀርታ፣

35. ዲሞናና ነህላል፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

36. ከሮቤል ነገድ፣ቦሶር፣ ያሀጽ፣

37. ቅዴሞትና ሜፍዓት፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤

38. ከጋድ ነገድ፣በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣

39. ሐሴቦንና ኢያዜር፣ እነዚህ አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፦

40. የሜራሪ ጐሣዎች ለሆኑት ለተቀሩት ሌዋውያን የተመደቡት ከተሞች ሁሉ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 21