ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 21:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እንደዚሁም ለነፍስ ገዳይ መማጠኛ የሆነችውን ኬብሮንንና ልብናን ከነ ማሰማሪያቸው ለካህኑ ለአሮን ልጆች ሰጧቸው፤

14. ደግሞም የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣

15. ሖሎንን፣ ዳቤርን፣

16. ዐይንን፣ ዮጣንና ቤትሳሚስን ከነ ማሰማሪያቸው ሰጧቸው፤ እነዚህ ዘጠኙ ከተሞች ከሁሉ ነገዶች ይዞታ ላይ ተከፍለው የተሰጡ ናቸው።

17. ከብንያም ነገድ ገባዖን፣ ጌባዕ፣

18. ዓናቶትና አልሞን የተባሉትን አራት ከተሞች ከነ ማሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።

19. ለካህናቱ ለአሮን ዝርያዎች ከነ ማሰማሪያቸው የተሰጧቸው ከተሞች ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

20. የሌዊ ልጅ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለሌሎቹ ደግሞ ከኤፍሬም ነገድ ላይ ተከፍለው የሚከተሉት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

21. በተራራማው በኤፍሬም ምድርም ለነፍሰ ገዳይ መማጠኛ የሆነችው ሴኬምና ጌዝር፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 21