ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 19:14-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በስተ ሰሜንም በኩል ወደ ሐናቶን ይዞርና በይፍታሕኤል ሸለቆ ላይ ይቆማል።

15. ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።

16. እነዚህ ሁሉ ለዛብሎን ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።

17. አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤

18. ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ኢይዝራኤል፣ ከስሎት፣ ሱነም፣

19. ሐፍራይም፣ ሺኦን፣ አናሐራት፣

20. ረቢት፣ ቂሶን፣ አቤጽ፣

21. ሬሜት፣ ዐይንጋኒም፣ ዐይንሐዳ እንዲሁም ቤትጳጼጽ።

22. ድንበራቸውም ታቦርና፣ ሻሕጹማን፣ ቤትሳሚስን ይነካና በዮርዳኖስ ላይ ያቆማል፤ እነዚህ ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ከተሞች ናቸው።

23. እነዚህ ለይሳኮር ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።

24. አምስተኛ ዕጣ ለአሴር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 19