ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢያሱ 14:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ስለዚህም ሙሴ በዚያች ዕለት፣ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ተከትለኸዋልና እግርህ የረገጣት ምድር ለዘላለም የአንተና የዘርህ ርስት ትሆናለች’ ብሎ ማለልኝ።

10. “አሁንም እነሆ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን ለሙሴ ከተናገረበት ጊዜ አንሥቶ እስራኤል በምድረ በዳ ሲንከራተት እኔን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት ጠብቆ አኑሮኛል፤ ይኸው ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።

11. ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም አብሮኝ አለ፤ ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድ ኀይሉም ብርታቱም አለኝ።

12. አሁንም እግዚአብሔር በዚያች ዕለት ቃል የገባልኝን ይህችን ኰረብታማ አገር ሰጠኝ። ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩና ከተሞቻቸውም ታላላቅና የተመሸጉ እንደሆኑ ያን ጊዜ አንተው ራስህ ሰምተሃል፤ ሆኖም ልክ እርሱ እንዳለው በእግዚአብሔር እርዳታ አሳድጄ አወጣቸዋለሁ።”

13. ከዚያም ኢያሱ የዮፎኒን ልጅ ካሌብን ባረከው፤ ኬብሮንንም ርስት አድርጎ ሰጠው።

14. ስለዚህም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኬብሮን የቄኔዛዊው የዮፎኒ ልጅ የካሌብ ርስት ሆነች፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ተከትሎአልና።

15. ኬብሮን ቀድሞ ከዔናቃውያን ሁሉ ታላቅ በሆነው በአርባቅ ስም ቂርያት አርባቅ ተብላ ትጠራ ነበር።ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢያሱ 14