እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ስለሰጣቸው ድል አደረጓቸው፤ በታላቂቱ ሲዶና መንገድ መጨረሻ እስከ ማስሮን፣ በስተ ምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዷቸው፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።