ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዩኤል 3:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ከገዛ ምድራቸው ልታርቋቸው፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋቸው።

7. “እነሆ፤ እነርሱን ከሸጣችሁባቸው ቦታዎች አነሣሣቸዋለሁ፤ እናንተም ያደረጋችሁትን በገዛ ራሳችሁ ላይ እመልስባችኋለሁ።

8. ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ለይሁዳ ሰዎች ሸጣለሁ፤ እነርሱም መልሰው በሩቅ ላሉት ለሳባ ሰዎች ይሸጧቸዋል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።

9. በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ለጦርነት ተዘጋጁ፤ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዩኤል 3