ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዩኤል 1:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የልጅነት እጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ።

9. የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጦአል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ካህናት ያለቅሳሉ።

10. ዕርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ምድሩም ደርቆአል፤እህሉ ጠፍቶአል፤አዲሱ የወይን ጠጅ አልቆአል፤ዘይቱም ተሟጦአል።

11. እናንት ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤እናንት የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤የዕርሻው መከር ጠፍቶአልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዩኤል 1