ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 9:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

7. ለመንግሥቱ ስፋት፣ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።

8. ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

9. ሕዝቡ በሙሉ፣ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎችይህን ያውቃሉ፤በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

10. “ጡቦቹ ወድቀዋል፤እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 9