ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 8:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እኔም፣ ካህኑን ኡሪያንንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ታማኝ ምስክሮቼ እንዲሆኑ እጠራቸዋለሁ።”

3. እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው።

4. ሕፃኑም፣ ‘አባባ’ ወይም ‘እማማ’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት፣ የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ይወሰዳል።”

5. እግዚአብሔርም እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረኝ፤

6. “ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰውንየሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣በረአሶንናበሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና።

7. ስለዚህ ጌታ ታላቁንና ብርቱውንየጐርፍ ውሃ፣የአሦርን ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ ሁሉ ያመጣባቸዋል።ውሃውም ከቦዩ ዐልፎ ተርፎበወንዙ ዳር ያለውን ምድር ሁሉ ያጥለቀልቃል፤

8. እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤እያጥለቀለቀ ያልፋል፤እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤አማኑኤል ሆይ፤የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከዳር ይሸፍናሉ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 8