ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 64:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አቤቱ፤ ሰማያትን ቀድደህ ምነው በወረድምነዋ ተራሮች በፊትህ በተናወጡ

2. እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ውሃንም እንደሚያፈላ፣ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ።

3. እኛ ያልጠበቅነውን አስፈሪ ነገር ባደረግህ ጊዜ፣አንተ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።

4. ከጥንት ጀምሮ፣በተስፋ ለሚጠባበቁት የሚደርስላቸው፣እንደ አንተ ያለውን አምላክ ያየ ዐይን፣ያደመጠ ጆሮ ፈጽሞ አልነበረም።

5. በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣እነሆ፣ ተቈጣህ፤ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?

6. ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 64