ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 56:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ፍትሕን ጠብቁ፤መልካሙን አድርጉ፤ማዳኔ በቅርብ ነው፤ጽድቄም ፈጥኖ ይገለጣልና።

2. ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣እነዚህን የሚፈጽም ሰው የተባረከ ነው።”

3. ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣“እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ጃንደረባም፣“እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

4. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ደስ የሚያሰኘኝን ለሚመርጡ፣ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ

5. በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ለዘላለም፣የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።

6. እርሱን ለማገልገል፣ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያቈራኙ መጻተኞች፣ የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣እርሱንም በማምለክ፣ሰንበትን ሳያረክሱ የሚያከብሩትን ሁሉ፣ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣

7. ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ።የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉየጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”

8. የተበተኑትን እስራኤል የሚሰበስብ፣ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ከተሰበሰቡት በተጨማሪ፣ሌሎችን እንደ ገና እሰበስባለሁ።”

9. እናንት የምድር አራዊት ሁሉ ኑ፤እናንት የዱር አራዊት ሁሉ ኑና በጥርሳቸሁ ቦጫጭቁ።

10. የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ዕውቀት የላቸውም፤ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤መጮኽ አይችሉም፤ተጋድመው ያልማሉ፤እንቅልፋሞች ናቸው።

11. እጅግ ሲበዛ ሆዳም ውሾች ናቸው፤ጠገብሁን አያውቁም፤የማያስተውሉ እረኞች ናቸው፤ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ሄዱ፤እያንዳንዳቸውም የግል ጥቅማቸውን ፈለጉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 56