ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 54:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ማንም ጒዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ጒዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።

16. “እነሆ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ አንጥረኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝአጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤

17. በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 54