ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 54:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. “አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።

12. ጒልላትሽን በቀይ ዕንቊ፣በሮችሽን በሚያብረቀርቁ ዕንቊዎች፣ቅጥሮችሽንም በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።

13. ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤የልጆችሽም ሰላም ታላቅ ይሆናል።

14. በጽድቅ ትመሠረቻለሽ፤የግፍ አገዛዝ ከአንቺ ይርቃል፤የሚያስፈራሽ አይኖርም፤ሽብር ከአንቺ ይርቃል፤አጠገብሽም አይደርስም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 54