ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 54:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “አንቺ መካን ሴት፤አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ባል ካላት ሴት ይልቅ፣የፈቷ ልጆች ይበዛሉና”ይላል እግዚአብሔር።

2. “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ፈጽሞ አትቈጥቢ፤ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ።

3. ወደ ቀኝም ወደ ግራም ትስፋፊያለሽ፤ዘሮችሽ መንግሥታትን ይወርሳሉ፤በባድማ ከተሞቻቸውም ይኖራሉና።

4. “አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

5. ባልሽ ፈጣሪሽ ነውና፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ታዳጊሽ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።

6. እንደ ተናቀች የልጅነት ሚስት፣ከልብ እንዳዘነችና እንደ ተጠላች ሚስት፣ እግዚአብሔር እንደ ገና ይጠራሻል”ይላል አምላክሽ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 54