ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 52:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።

14. ብዙዎች በእርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣መልኩ ከማንም ከሰው የተለየ፤ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።

15. ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤በእርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ያልሰሙትን ያስተውላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 52