ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 52:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ኀይልን ልበሺ፤ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ!የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ያልተገረዘ የረከሰምከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።

2. ትቢያሽን አራግፊ፤ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ።

3. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”

4. ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በመጀመሪያ ሕዝቤ ይኖር ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤በኋላም አሦር ያለ ምክንያት አስጨንቆ ገዛው።

5. “አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር፤“ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዶአል፤የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል”ይላል እግዚአብሔር።“ቀኑን ሙሉ፣ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል።

6. ስለዚህ ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤በዚያ ቀንም፣አስቀድሜ የተናገርሁ እኔ መሆኔን ይረዳል፤እነሆ፤ እኔው ነኝ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 52