ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 41:4-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው?እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ከኋለኛውም ጋር፤ እኔው ነኝ።”

5. ደሴቶች አይተው ፈሩ፤የምድር ዳርቾች ደነገጡ፤ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።

6. እያንዳንዱ ይረዳዳል፤ወንድሙንም፣ “አይዞህ” ይለዋል።

7. ባለጅ የወርቅ አንጥረኛውን ያበረታታዋል፤በመዶሻ የሚያሳሳውም፣በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያነቃቃዋል፤ስለ ብየዳም ሥራው፣ “መልካም ነው” ይለዋል፤የጣዖቱ ምስል እንዳይወድቅም በምስማር ያጣብቀዋል።

8. “አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣የመረጥሁ ያዕቆብ፣የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፤

9. ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ከአጥናፍም የጠራሁህ፣‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤መረጥሁህ እንጂ፤ አልጣልሁህም።

10. እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

11. “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤የሚቋቋሙህ፣እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።

12. ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣አታገኛቸውም፤የሚዋጉህም፣እንዳልነበሩ ይሆናሉ።

13. እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ‘አትፍራ፤እረዳሃለሁ’ብዬ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 41