ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 40:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ይላል አምላካችሁ።

2. ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ዐውጁላትም፤በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቶአል፤የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሎአል፤ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።

3. የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤“የእግዚአብሔርን መንገድ፣በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣በበረሓ አስተካክሉ።

4. ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፤ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ወጣ ገባው ምድር ይስተካከላል፤ሰርጓጒጡም ሜዳ ይሆናል።

5. የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፤ሰው ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።”

6. ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ።“ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።

7. ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነፍሶበታልና፤ሕዝቡ በርግጥ ሣር ነው።

8. ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

9. አንተ ለጽዮን የምሥራችን የምትነግር፤ከፍ ወዳለው ተራራ ውጣ፤አንተ ለኢየሩሳሌም ብሥራት የምትነግር፣ድምፅህን ከፍ አድርገህ ጩኽ።ከፍ አድርገው፤ አትፍራ፤ለይሁዳም ከተሞች፣“እነሆ፤ አምላካችሁ!” በል።

10. እነሆ፤ ልዑል እግዚአብሔር በኀይልይመጣል፤ክንዱ ስለ እርሱ ይገዛል።እነሆ፤ ዋጋው ከእርሱ ጋር ነው፤የሚከፍለውም ብድራት አብሮት አለ።

11. መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ጠቦቶቹን በክንዱ ይሰበስባል፤በዕቅፉም ይይዛቸዋል፤የሚያጠቡትንም በጥንቃቄ ይመራል።

12. ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ተራሮችን በሚዛን፣ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው?

13. የእግዚአብሔርን መንፈስ የተረዳ፣አማካሪውስ ሆኖ ያስተማረው ማነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 40