ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 39:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው።ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ።

5. ኢሳይያስም ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤

6. ‘እነሆ፤ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹትም ሁሉ ወደ ባቢሎን ተማርኮ የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፤ አንዳች የሚተርፍ ነገር የለም፤ ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 39