ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 38:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. “እግዚአብሔር ሆይ፤ በፊትህ በታማኝነትና በፍጹም ልብ ደስ የሚያሰኝህንም በማድረግ እንዴት እንደኖርሁ አቤቱ አስብ።” ሕዝቅያስም አምርሮ አለቀሰ።

4. የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

5. “ሂድና ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ።

6. አንተንና ይህቺን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ለከተማዋም እከላከልላታለሁ።

7. “ ‘እግዚአብሔር የገባልህን ቃል እንደሚፈጽምልህ፣ የእግዚአብሔር ምልክት ይህ ነው፤

8. በአካዝ የሰዓት መቍጠሪያ ደረጃ ላይ፣ የወረደውን የፀሓይ ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።’ ” ስለዚህ ወርዶ የነበረው የፀሓይ ጥላ ያንኑ ያህል ወደ ኋላ ተመለሰ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 38