ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 38:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እነሆ፤ በሥቃይ የተጨነቅሁት፣ለጥቅሜ ሆነ፤ከጥፋት ጒድጓድ፣በፍቅርህ ጠበቅኸኝ፤ኀጢአቴንም ሁሉ፣ወደ ኋላህ ጣልኽ።

18. ሲኦል አያመሰግንህም፤ሞት አያወድስህም፤ወደ ጒድጓድ የሚወርዱ፣የአንተን ታማኝነት ተስፋ አያደርጉም።

19. እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል።ስለ አንተ ታማኝነትም፣አባቶች ለልጆቻቸው ይነግራሉ።

20. እግዚአብሔር ያድነኛል፤ስለዚህ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።

21. ኢሳይያስም፣ “የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳችሁ በዕባጩ ላይ አድርጉለት እርሱም ይፈወሳል” ብሎ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 38