ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 37:34-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ወደዚች ከተማም አይገባም”ይላል እግዚአብሔር።

35. “ስለ ራሴና፣ ስለ አገልጋዬም ስለ ዳዊት፣ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ፤ አድናታለሁም።”

36. ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰው ገደለ፤ በሰፈር ያሉት ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።

37. ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም አመለጠ፤ ወደ ነነዌም ተመልሶ በዚያ ተቀመጠ።

38. ሰናክሬም በአምላኩ በናሳራክ ቤተ ጣዖት በሚሰግድበት ጊዜ፣ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም ወደ አራራት ምድር ኰበለሉ፤ ልጁም አስራዶን በምትኩ ነገሠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 37