ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 37:30-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤“በዚህ ዓመት የገቦውን፣በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

31. እንደ ገናም የይሁዳ ቤት ቅሬታ፣ሥሩን ወደ ታች ይሰዳል፤ ከላይም ፍሬ ያፈራል፤

32. ቅሬታ የሆኑት ከኢየሩሳሌም፣የተረፉትም ከጽዮን ተራራ ይመጣሉና፤የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።

33. “ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤“ወደዚች ከተማ አይገባም፤ፍላጻ አይወረውርባትም፤ጋሻ አንግቦ አይመጣባትም፤በዐፈር ቍልልም አይከባትም።

34. በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ወደዚች ከተማም አይገባም”ይላል እግዚአብሔር።

35. “ስለ ራሴና፣ ስለ አገልጋዬም ስለ ዳዊት፣ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ፤ አድናታለሁም።”

36. ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰው ገደለ፤ በሰፈር ያሉት ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።

37. ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም አመለጠ፤ ወደ ነነዌም ተመልሶ በዚያ ተቀመጠ።

38. ሰናክሬም በአምላኩ በናሳራክ ቤተ ጣዖት በሚሰግድበት ጊዜ፣ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም ወደ አራራት ምድር ኰበለሉ፤ ልጁም አስራዶን በምትኩ ነገሠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 37