ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 37:28-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. “ ‘እኔ ግን የት እንዳለህ፣መምጣት መሄድህ ምን ጊዜ እንደሆነ፣በእኔም ላይ እንዴት በቍጣ እንደም ትነሣሣ ዐውቃለሁ።

29. በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣በአፍንጫህ ስናጌን፣በአፍህ ልጓሜን አገባለሁ፤በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስአደርግሃለሁ።’

30. “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤“በዚህ ዓመት የገቦውን፣በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

31. እንደ ገናም የይሁዳ ቤት ቅሬታ፣ሥሩን ወደ ታች ይሰዳል፤ ከላይም ፍሬ ያፈራል፤

32. ቅሬታ የሆኑት ከኢየሩሳሌም፣የተረፉትም ከጽዮን ተራራ ይመጣሉና፤የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።

33. “ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤“ወደዚች ከተማ አይገባም፤ፍላጻ አይወረውርባትም፤ጋሻ አንግቦ አይመጣባትም፤በዐፈር ቍልልም አይከባትም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 37