ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 35:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤እንደ አደይም ያብባል።

2. በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል።የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።

3. የደከሙትን እጆች አበርቱ፤የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ፤

4. የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤“በርቱ፤ አትፍሩ፤አምላካችሁ ይመጣል፤ሊበቀል ይመጣል፤እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ሊያድናችሁ ይመጣል።”

5. በዚያን ጊዜም የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ፤የደንቈሮም ጆሮዎች ይከፈታሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 35