ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 34:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።

11. ጭልፊትና ጃርት ይወርሷታል፤ጒጒትና ቍራም ጐጆ ይሠሩባታል።እግዚአብሔር በኤዶም ላይ፣የመፈራረሷን ገመድ፣የመጥፊያዋንም ቱንቢ ይዘረጋል።

12. መሳፍንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ።

13. በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤የቀበሮዎች ጒድጓድ፣የጒጒቶችም መኖሪያ ትሆናለች።

14. የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋር አብረው ይሆናሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።

15. ጒጒት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿትታቀፋቸዋለች፤ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።

16. በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውንተመልከቱ፤ አንብቡም፤ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቶአል፤መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።

17. ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች።ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 34