ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 33:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣አንት አጥፊ፣ ወዮልህ!አንተ ሳትካድ የምትክድ፣አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ!ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ትጠፋለህ፤ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ።

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረን፤አንተን ተስፋ አድርገናል።በየማለዳው ብርታት፣በጭንቅ ጊዜም ድነት ሁነን።

3. ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፣መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።

4. ሕዝቦች ሆይ፤ አንበጣ እንደሚሰበስብ ብዝበዛችሁም ይሰበሰባል፤ሰዎችም እንደ ኩብኩባ ይጨፍሩበታል።

5. እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።

6. እርሱ ለዘመንህ የሚያስተማምን መሠረት፣የድነት፣ የዕውቀትና የጥበብ መዝገብ ይሆናል፤ እግዚአብሔርንም መፍራት የዚህ ሀብት ቍልፍ ነው።

7. እነሆ፤ ጐበዞቻቸው በየመንገዱ ይጮኻሉ፤የሰላም መልእክተኞችም አምርረው ያለቅሳሉ።

8. አውራ ጐዳናዎች ባዶ ናቸው፤በመንገድ ላይ ሰው የለም፤ስምምነቱ ፈርሶአል፤መካሪዎቹ ተንቀዋል፤የሚከበርም የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 33