ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 32:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያዳምጣሉ።

4. የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤አጥርቶም ይናገራል።

5. ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ጋጠወጥም አይከበርም።

6. ሰነፍ ስንፍናን ይናገራል፤አእምሮው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌለበትን አድራጐት ይፈጽማል፤ በእግዚአብሔርም ላይ የስሕተት ቃል ይናገራል፤ለተራበ ምግብ ይከለክላል፤ለተጠማ ውሃ አይሰጥም።

7. የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ክፋት ያውጠነጥናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 32