ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 32:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፣ምድረ በዳው ለም መሬት፣ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው።

16. በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤

17. የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም መታመን ይሆናል።

18. ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣በሚያስተማምን ቤት፣ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

19. ደኑ በበረዶ ቢመታ፣ከተማውም ፈጽሞ ቢወድም፣

20. በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ምንኛ የተባረካችሁ ናችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 32