ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 32:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ስለ ለሙ መሬት ደረታችሁን ምቱ፤ስለ ፍሬያማው የወይን ተክል ዕዘኑ፤

13. ስለ ሕዝቤ ምድር፣እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ።

14. ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤

15. ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፣ምድረ በዳው ለም መሬት፣ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው።

16. በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 32