ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 3:21-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. የጣት ቀለበቶችንና የአፍንጫ ቀለበቶችን፣

22. ያማረውን ቀሚስ፣ የውስጥ ልብሱን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣

23. መስታወቱን፣ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፣ የራስ ጌጡን፣ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።

24. በሽቶ ፈንታ ግማት፣በሻሽ ፈንታ ገመድ፣አምሮ በተሠራ ጠጒር ፈንታ ቡሀነት፣ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል።

25. ወንዶቻችሁ በሰይፍ ስለት፣ተዋጊዎቻችሁ በጦርነት ይወድቃሉ።

26. የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 3