ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 23:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በታላላቅ ውሆች ላይ፣ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤የዐባይ መከር ገቢዋ ነበር፤እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።

4. አንቺ ሲዶና ሆይ፣አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፣ ዕፈሪ፤ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሎአልና።

5. ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።

6. እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤

7. እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣የተድላ የደስ ከተማችሁ ይህች ናትን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 23