ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 21:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ከምድረ በዳ ይመጣል።

2. የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል።ኤላም ሆይ፤ ተነሺ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢእርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።

3. ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።

4. ልቤ ተናወጠ፤ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤የጓጓሁለት ውጋጋን፣ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 21