ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 21:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ከምድረ በዳ ይመጣል።

2. የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል።ኤላም ሆይ፤ ተነሺ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢእርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።

3. ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።

4. ልቤ ተናወጠ፤ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤የጓጓሁለት ውጋጋን፣ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ።

5. ማእዱን አሰናዱ፤ምንጣፉን አነጠፉ፤በሉ፤ ጠጡ!እናንት ሹማምት ተነሡ፤ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!

6. ጌታ እንዲህ አለኝ፤“ሂድ፤ ጠባቂ አቁም፤ያየውንም ይናገር፤

7. በፈረሶች የሚሳብ፣ሠረገሎችን ሲያይ፣በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ያስተውል፣በጥንቃቄም ያስተውል።”

8. ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤“ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።

9. እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብበሠረገላ መጥቶአል፤እንዲህም ሲል መለሰ፣‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀየአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ።’ ”

10. በዐውድማ ላይ የተወቃህ ሕዝቤ ሆይ፤ከሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ከእስራኤል አምላክ፣የሰማሁትን እነግርሃለሁ።

11. ስለ ኤዶም የተነገረ ንግር፤አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣“ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ።

12. ጠባቂውም መለሰ፤“ይነጋል፤ ግን ተመልሶ ይመሻል፤መጠየቅ ከፈለጋችሁ፣ ጠይቁ፤ነገር ግን ተመልሳችሁ ኑ” አለ።

13. ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 21