ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 2:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

17. የሰው እብሪት ይዋረዳል፤የሰውም ኵራት ይወድቃል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤

18. ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።

19. እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱከግርማውም የተነሣ፣ወደ ዐለት ዋሻወደ መሬትም ጒድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።

20. በዚያን ቀን ሰዎችሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውንለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

21. እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱእንዲሁም ከግርማው የተነሣ፣ወደ ድንጋይ ዋሻ፣ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።

22. እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለችበሰው አትታመኑ፤ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 2