ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 2:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ከፍ ያለው ኰረብታ ሁሉ፣

15. ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፣የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣

16. የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

17. የሰው እብሪት ይዋረዳል፤የሰውም ኵራት ይወድቃል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤

18. ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።

19. እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱከግርማውም የተነሣ፣ወደ ዐለት ዋሻወደ መሬትም ጒድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 2