ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 19:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ግብፅ የተነገረ ንግር፤እነሆ፤ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ላይ ተቀምጦወደ ግብፅ ይመጣል፤የግብፅ ጣዖቶች በፊቱ ይርዳሉ፤የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።

2. “ግብፃዊውን በግብፃዊው ላይ አስነሣለሁ፤ወንድም ወንድሙን፣ባልንጀራ ባልንጀራውን፣ከተማም ከተማን፣መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።

3. የግብፃውያን ልብ ይሰለባል፤ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤እነርሱም ጣዖታትንና የሙታንን መናፍስት፤መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ምክር ይጠይቃሉ።

4. ግብፃውያንን አሳልፌ፣ለጨካኝ ጌታ ክንድ እሰጣቸዋለሁ፤አስፈሪ ንጉሥም ይገዛቸዋል”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

5. የዐባይ ወንዝ ይቀንሳል፤ውሃውም እየጐደለ ይሄዳል።

6. መስኖዎቹ ይከረፋሉ፤የግብፅ ጅረቶች ይጐድላሉ፤ ይጠፋሉም።ደንገሉና ቄጠማውም ይጠወልጋል፤

7. እንዲሁም በዐባይ ዳር፣በወንዙ መፋሰሻ ላይ ያሉት ተክሎች ይጠወልጋሉ።በዐባይ ዳር የተዘራው ዕርሻ ሁሉ፣በነፋስ ይወሰዳል፤ ምንም አይቀርም።

8. ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤በዐባይ ወንዝ ላይ መንጠቆአቸውን የሚወረውሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤በውሃ ላይ መረባቸውን የሚጥሉ ሁሉ፣ጒልበታቸው ይዝላል።

9. የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ።

10. ልብስ ሠሪዎች ያዝናሉ፤ደመወዝተኞችም ልባቸው ይሰበራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 19