ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 13:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

4. በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣የሚሰማውን ጩኸት አድምጡበመንግሥታትም መካከል፣እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ!የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።

5. እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።

6. የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።

7. ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 13