ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢሳይያስ 13:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ንግር፤

2. በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፣በእጅ ምልክት ስጡ።

3. በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

4. በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣የሚሰማውን ጩኸት አድምጡበመንግሥታትም መካከል፣እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ!የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።

5. እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።

6. የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።

7. ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።

8. ሽብር ይይዛቸዋል፤ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።

9. እነሆ፤ የእግዚአብሔር ቀን ጨካኝ ነው፤ምድርን ባድማ ሊያደርጋት፣በውስጧም ያሉትን ኀጢአተኞች ሊያጠፋ፣ከመዓትና ከብርቱ ቍጣ ጋር ይመጣል።

10. የሰማይ ከዋክብትና ሰራዊታቸው፣ብርሃን አይሰጡም፤ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢሳይያስ 13