ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አብድዩ 1:14-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፣በጭንቀታቸው ቀን፣የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።

15. “በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሶአል፤አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

16. እናንተ በቅዱሱ ተራራዬ እንደ ጠጣችሁ፣አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ፤ይጠጣሉ፤ አብዝተውም ይጠጣሉ፤ከዚህም በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።

17. ነገር ግን በጽዮን ተራራ ነጻ መውጣት ይሆናል፤የያዕቆብ ቤትም እርሷ የተቀደሰች ትሆናለች፤ርስታቸውን ይወርሳሉ።

18. የያዕቆብ ቤት እሳት፣የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ከዔሳው ቤት የሚተርፍ፣ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሮአል።

19. የኔጌብ ሰዎች፣የዔሳውን ተራራ ይይዛሉ፤ከተራራው ግርጌ ያሉ ሰዎችም፣የፍልስጥኤማውያንን ምድር ይወርሳሉ፤የኤፍሬምንና የሰማርያንም ዕርሻ ይይዛሉ፤ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።

20. በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣እስከ ሰራጵታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።

21. የዔሳውን ተራሮች ለመግዛት፣ነጻ አውጪዎች ወደ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አብድዩ 1