ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አስቴር 7:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ንጉሡ ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ሲመለስ አስቴር ደገፍ ባለችበት ድንክ ዐልጋ ላይ ሐማ ተደፍቶ ነበር።ንጉሡም፣ “ይባስ ብሎ አብራኝ ያለችውን ንግሥት በገዛ ቤቴ ሊደፍራት ያስባልን?” ሲል ተናገረ።ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ ገና እንደ ወጣ፣ የሐማን ፊት ሸፈኑት።

9. ከዚያም ንጉሡን በቅርብ ከሚያገለግሉት ጃንደረቦች አንዱ የሆነው ሐርቦና፣ “እነሆ ቁመቱ አምሳ ክንድ የሆነ ግንድ በሐማ ቤት አጠገብ ተተክሎአል፤ ይህን ያዘጋጀው ንጉሡን ለማዳን በጎ ነገር ለተናገረው ለመርዶክዮስ ነው” አለ።ንጉሡም፣ “በዚሁ ላይ ስቀሉት” አለ።

10. ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቊጣ በረደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አስቴር 7