ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አስቴር 3:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ንጉሡም ሐማን፣ “ገንዘቡን እዚያው ያዘው፤ ሕዝቡንም እንዳሻህ አድርገው” አለው።

12. ከዚያም በመጀመሪያው ወር ዐሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሓፊዎች ተጠሩ። እነርሱም የሐማን ትእዛዝ በሙሉ በየአውራጃው ፊደልና በየሕዝቡ ቋንቋ፣ ለንጉሡ እንደራሴዎች፣ ለልዩ ልዩ አውራጃ ገዦችና ለልዩ ልዩ ሕዝቦች መኳንንት ጻፉ። ይህም የተጻፈው በራሱ በንጉሡ ጠረክሲስ ስም ሲሆን፣ የታተመውም በራሱ ማኅተም ነበር።

13. አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ሕፃን ሳይባል አይሁድ ሁሉ በዚያኑ ዕለት እንዲጠፉ፣ እንዲገደሉና እንዲደመሰሱ፣ ሀብታቸውም እንዲዘረፍ ደብዳቤ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ በመልእክተኞች እጅ ተላከ።

14. ለእያንዳንዱም አውራጃ ሕዝብ እንዲታወቅ፣ እነርሱም ለዚያ ቀን ዝግጁ እንዲሆኑ፣ የዋናው ዐዋጅ ቅጅ ሕግ እንዲወጣና ወደ እያንዳንዱም አውራጃ እንዲላክ ተደረገ።

15. መልእክተኞቹ በንጉሡ ትእዛዝ ተቻኵለው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተላለፈ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፤ የሱሳ ከተማ ግን ግራ ተጋብታ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አስቴር 3