ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አስቴር 1:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. በዚህች በዛሬዪቱም ዕለት የንግሥቲቱን አድራጎት የሰሙ የፋርስና የሜዶን መኳንንት ሚስቶች፣ ለንጉሡ መኳንንት ሁሉ በዚሁ ዐይነት ሊመልሱ ነው፤ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ማብቂያ የሌለው ንቀትና ጠብ ይፈጠራል።

19. “ስለዚህ ነገሩ ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ፣ አስጢን ወደ ንጉሡ ወደ ጠረክሲስ ዘንድ ከእንግዲህ ወዲህ ፈጽሞ እንዳትገባ ንጉሣዊ ዐዋጅ ይውጣ፤ ይህም የማይሻር ሆኖ በፋርስና በሜዶን ሕጎች ይጻፍ፤ እንዲሁም ንጉሡ የእቴጌነቷን ክብር ከእርሷ ለምትሻል ለሌላዪቱ ይስጥ።

20. ከዚያም የንጉሡ ዐዋጅ በሰፊው ግዛቱ ሁሉ ሲነገር፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ያሉት ሴቶች ሁሉ ባሎቻቸውን ያከብራሉ።”

21. ንጉሡና መኳንንቱ ሁሉ በዚህ ምክር ተደሰቱ፤ ንጉሡም ምሙካ ያቀረበውን ሐሳብ በሥራ ላይ አዋለው።

22. እያንዳንዱ ሰው በራሱ ቤተ ሰብ ላይ ገዥ እንዲሆን መልእክት አስተላለፈ፤ መልእክቱም ለየአውራጃዎቹ በየራሳቸው ጽሑፍና ለእያንዳንዱ ሕዝብ በየራሱ ቋንቋ ተጽፎ በግዛቱ ሁሉ ተበተነ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አስቴር 1