ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

አሞጽ 5:4-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”

5. ቤቴልን አትፈልጉ፤ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ጌልገላ በእርግጥ ትማረካለች፤ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና።

6. እግዚአብሔርን ፈልጉ፤በሕይወትም ትኖራላችሁ፤አለበለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።

7. እናንት ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!

8. ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስ፣ስሙ እግዚአብሔር ነው፤

9. እርሱ በብርቱው ላይ ድንገተኛ ጥፋትን፣በተመሸገውም ከተማ ላይ ውድመትን ያመጣል።

10. እናንተ በፍርድ አደባባይየሚገሥጻችሁን ትጠላላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ትንቃላችሁ።

11. እናንተ ድኻውን ትረግጣላችሁ፤እህል እንዲሰጣችሁም ታስገድዱታላችሁ፤ስለዚህ በተጠረበ ድንጋይ ቤት ብትሠሩም፣በውስጡ ግን አትኖሩም፤ባማሩ የወይን ተክል ቦታዎች ወይን ብትተክሉም፣የወይን ጠጁን ግን አትጠጡም፤

12. ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደሆነ፣በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና።ጻድቁን ትጨቊናላችሁ፤ጒቦም ትቀበላላችሁ፤በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።

13. ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።

14. በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፣መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራችሁት፣የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል።

15. ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ፤ምናልባትም የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር፣ለዮሴፍ ትሩፍ ይራራ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ አሞጽ 5